የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኀበር በሰላማዊ ሰልፍ ላይ ሰብዓዊ እርዳታ አደረገ፣ ሕይወት አዳነ
June 26, 2018
የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማzበር ቅዳሜ ሰኔ 16 ቀን 2010 ዓ.ም በተካሄደ የምስጋናና የድጋፍ ሰልፍ ላይ አስቀድሞ በመዘጋጀት በ9 ጊዜያዊ ጣቢያዎች፣ 13 አምቡላንሶችና 80 በጐ ፈቃደኞችን ከጠዋቱ 11፡00 ሰዓት ጀምሮ በማሠማራት ለበርካታ ወገኖቻችን የመጀመሪያ ሕክምና ዕርዳታ በመስጠት እና ወደ አቅራቢያ ሆስፒታሎች በማጓጓዝ ሕይወትን የማዳን ሰብዓዊ ተግባር ሲያከናውን ውሏል፡፡
እንደወትሮው የመጨናነቅ፣ የአየር እጥረት፣ የድካም እና በመውደቅ አደጋ ለደረሰባቸው ሠልፈኞች እርዳታ ሲሰጥ የነበረው የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማzበር፣ በዕለቱ በተከሰተው የቦንብ ፍንዳታ አቅራቢያ ያሠማራቸው አምስት አምቡላንሶችና የመጀመሪያ ሕክምና የሚሰጡ በጐ ፈቃደኞች ለ50 ሰዎች በራሱ ጣቢያ የመጀመሪያ ደረጃ የሕክምና እርዳታ በማድረግ የሸኘ ሲሆን 114ቱን ደግሞ ወደ ጥቁር አንበሳ፣ ዘውዲቱና አለርት ሆስፒታሎች በማጓጓዝ ሕይወት የመታደግ አኩሪ ሰብዓዊ ተግባር በማከናወን በአጠቃላይ ለ164 ተጐጂዎች የሕክምና እርዳታ ሰብዓዊ አገልግሎት አበርክቷል፡፡
ሁለት የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማzበር በጐ ፈቃደኞች መጠነኛ ጉዳት ደርሶባቸው ታክመዋል፡፡
ማzበሩ ይህንን ሰብዓዊ ተግባር ሲያከናውን የዋለው አራት በፒያሳ፣ በጦርኃይሎች፣ በጐተራና በመገናኛ ጣቢያዎች እንዲሁም አራቱ በመስቀል አደባባይ ዙሪያ በአራቱ መውጫዎች ማለትም በአዲስ አበባ ሙዚየም አካባቢ፣ በስታዲዮም አካባቢ /ደብረዘይት መውጫ/ ግዮን ፊት ለፊትና በዋናው ጽ/ቤት በአጠቃላይ በ8 ጊዜያዊ የመጀመሪያ ህክምና ጣቢያዎች በመታገዝ ነበር፡፡
ቅድሚያ ለሰብዓዊነት በሚል መርህ የሚንቀሳቀሰው አንጋፋ፣ ገለልተኛ፣ ያለአድልኦ በተፈጥሮና በሰው ሠራሽ አደጋዎች ለተጐዱ ሰዎች በነፃነት ሰብዓዊ አገልግሎት የሚሠጠው የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማzበር ሐምሌ 1 ቀን 2010 ዓ.ም 83ኛ ዓመቱን ያከብራል፡፡