TOLL FREE NUMBER: 907

  • Donate
HealthFlex
×
  • Home
  • Who We Are
    • About us
    • Patron
    • Governance
    • Where We Work
  • What We Do
    • Disaster Risk Management
    • Peace Building
    • Volunteers & Membership
    • Image Building
    • Capacity Building
    • Resource Mobilization
  • Get Involved
    • Donate
    • Be a Volunteer
    • Be a Member
    • CCDHS
    • Vacancy
    • Procurement
  • Media Hub
    • News
    • Publication
    • Events
    • Gallery
      • Photos
      • Videos
  • Get help
    • Restoring Family Links
    • Ambulance Services
    • E-Learning
    • Mobile App
  • Contact

ኢቀመማ የህብረተሰቡን አደጋ የመቋቋም አቅም ለመገንባት የሰራቸው ሥራዎች አበረታች እንደነበሩ አስታወቀ

September 10, 2018

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር (ኢቀመማ) ነሀሴ 25 ቀን 2011 ዓ.ም በሀዋሳ ከተማ ባካሄደው ጠቅላላ ጉባኤ በ2010 የበጀት ዓመት ከ92 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ለሆኑ የህብረተሰቡ ክፍሎች የአደጋ ምላሽ እና ከአደጋ በኋላ የማቋቋም ሥራዎችን አከናውኗል፡፡ በበጀት ዓመቱ ለ297 ሺህ አባዎራዎች የመጀመሪያ ደረጃ እርዳታ ድጋፍ ለመስጠት በማቀድ 599 ሺህ በላይ ቤተሰቦችን ተጠቃሚ በማድረግ እቅዱን ከእጥፍ በላይ ማሳካት ችሏል፡፡

ማኅበሩ በምዕራብ ጉጂና ጌዲኦ፣ በጅግጅጋ፣ በሶማሊያ፣ ኦሮሚያ እና በሌሎች በተለያዩ አካባቢዎች የደረሱ ግጭችን ተከትሎ ለተፈናቀሉ ወገኖች ምግብ እና ምግብ ነክ ቁሳቁሶች ድጋፍ አድርጓል፡፡

ኢቀመማ ህብረተሰቡን ከአደጋ በኋላ ለማቋቋም በዘረጋቸው 9 ፕሮጀክቶች አማካኝነት ከ28 ሺህ 500 በላይ አባወራዎች (142 500) በላይ ሰዎችን በመደገፍ የዕቅዱን 99 በመቶ እንዳስፈፀመ አስታውቋል፡፡ አደጋን አስቀድሞ በመከላከል እና በተለያዩ የልማት ተግባራት ማለትም የግብርና ሥራ እና የምርጥ ዘር አቅርቦት፣ የኑሮ ማሻሻያ እና የአቅም ማጠናከሪያ ሥራዎች፣ የጤና እና ንፅህና አጠባበቅ ድጋፎች፣ መሰረታዊ መድሃኒቶችን ማሰራጨት ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡

ጉባኤው ሌሎች በበጀት ዓመቱ ታቅደው የነበሩ ተግባራትንና አፈፃፀማቸውን በመገምገም መሻሻል እና ተጠናክሮ መቀጠል ይገባቸዋል የተባሉ ጉዳዮችን ለመለየት ያስቻለ ሲሆን፤ የትኩረት አቅጣጫዎችን አመላክቷል፡፡ የአደጋ ጊዜ የመጠባበቂያ ቁሳቁስ በሚፈለገው መጠን በመጋዘን አለመያዝ በዓመቱ ካጋጠሙ ችግሮች መካከል ተጠቅሷል፡፡ የቅንጅትና የትብብር ሥራ፣ አቅም ግንባታ እና ወጪ ቅነሳ ማህበሩ በቀጣይ ትኩረት የሚያደርግባቸው ጉዳዮች ናቸው፡፡

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ለክልሉ የቀይ መስቀል ቅርንጫፍ ፅ/ቤት በየዓመቱ የ500 ሺህ ብር ድጋፍ ለማድረግ መወሰኑ የሚበረታታ እንደሆነ ተገልጿል፡፡ በተመሳሳይ በበጀት ዓመቱ ለህብረተሰቡ ፈጥኖ በመድረስ እና አደጋን በመከላከል በኩል የላቀ አፈፃፀም ላስመዘገቡ ክቅርንጫፍ ፅ/ቤቶች የዕውቅና ሽልማት የተበረከተ ሲሆን፤ ከትላልቅ ክልሎች አማራ እና ኦሮሚያ፤ ከታዳጊ ክልሎች የቤኒሻንጉል እና ሀረሪ ቅርንጫፍ ፅ/ቤቶች ተሸላሚዎች ሆነዋል፡፡

በጠቅላላ ጉባኤው ከብሄራዊ ፅ/ቤት እና ክልል ቅርንጫፍ ፅ/ቤቶች የተውጣጡ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች እንዲሁም የክልል እና ብሔራዊ ቦርድ አመራሮች ተሳትፈዋል፡፡ በተጨማሪም የሞያሌ ልዩ ወረዳ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት በስብሰባው ላይ በልዩ ሁኔታ ተገኝቷል፡፡

Calendar

September 2018
M T W T F S S
 12
3456789
10111213141516
17181920212223
24252627282930
« Aug   Oct »

Categories

  • News
  • Uncategorized

Tag Cloud

Front Page

Contact Us

Ethiopian Red Cross Society Headquarter

+251-115-18-01-83

ercsinfo@redcrosseth.org

P.O.Box: 195

Ras Desta Dametew Avenue, Addis Ababa, Ethiopia

Quick Links

  • Donate
  • Be a Volunteer
  • Be a Member
  • Vacancy
  • Procurement
  • Partners link
  • FAQ

FOLLOW US

  • Facebook
  • YouTube
  • X
  • Telegram
  • Flickr
Copyright ©2025 | All Rights Reserved
Designed and Developed By Rackmint System
X