ማኅበሩ በአምስት ዓመት ስትራቴጂካዊ ዕቅዱ ዙሪያ ውይይት አካሄደ

ማኅበሩ በአምስት ዓመት ስትራቴጂካዊ ዕቅዱ ዙሪያ ውይይት አካሄደ
የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ከብሔራዊ ጽ/ቤቱና በየደረጃው ከሚገኙ የማኅበሩ አመራር አካላት ጋር በአምስት ዓመቱ ስትራቴጂካዊ ዕቅድ አተገባበር ዙሪያ ሰፊ ውይይት ያደረገ ሲሆን ዕቅዱን ተግባራዊ ለማድረግና የሚጠበቀውን ውጤት ለማስመዝገብ የማህበሩ አመራርና ሰራተኞች ዕቅዱን በአግባቡ ተገንዝበው በኃላፊነት ስሜትና በትኩረት መስራት እንደሚጠበቅባቸው ተጠቁሟል፡፡

የማኀበሩ ዋና ጸሐፊ አቶ አበራ ሉሌሳ እንደተናገሩት አገራዊና ዓለም አቀፋዊ ነባራዊ ሁኔታን ባገናዘበ መልኩ ተቋማዊ ትራንስፎረሜሽን ማምጣት አስፈላጊ መሆኑን አንስተው ይህንን ለውጥ እውን ለማድረግ ቁርጠኝነትና ትራስፎርሜሽኑ የሚጠይቀውን መስዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁነትን ይጠይቃል ብለዋል፡፡
አቶ አበራ አክለውም በየደረጃው ያለ አመራር በስምንቱ የዕቅዱ አምዶች ላይ የጠራ ግንዛቤ በመያዝና ከራሱ ጋር በማዋሃድ በስሩ ላለው የማህበሩ ሰራተኛ እቅዱን ማስተዋወቅ ፤ማወያየትና በቂ ግንዛቤ መያዙን ማረጋገጥ እንደሚጠበቅበት አሳስበዋል፡፡

የክልልና ፤የዞንና የወረዳ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊዎችም ዕቅዱ ከዝግጅቱ ጀምሮ በበቂ ጥናትና አሳታፊነት ላይ ተመስርቶ መዘጋጀቱን አንስተው በቀጣይ አምስት አመታት ውስጥ ማኅበሩን አንድ ርምጃ ወደፊት ማራመድ እንደሚችል የገለጹ ሲሆን ለዕቅዱ ተግባራዊነት ቁርጠኛ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

በመርሃ ግብሩ ማጠናቀቂያ ላይም በየደረጃው የሚገኙት የስራ ሃላፊዎች ለስትራቴጂክ ዕቅዱ ተግባራዊነት ያላቸውን ቁርጠኝነት የቡድን ቻርተር በመፈራረም ገልጸዋል፡፡