TOLL FREE NUMBER: 907

  • Donate
HealthFlex
×
  • Home
  • Who We Are
    • About us
    • Patron
    • Governance
    • Where We Work
  • What We Do
    • Disaster Preparedness and Response
    • Disaster Risk Reduction and Community Resilience
    • Health and Wellbeing
    • Members, Volunteer and Youth Engagement and Management
    • Humanitarian Diplomacy and Communication
    • Partnership Development and Management
    • Institutional and Leadership Transformation
    • Resource Development, Mobilization and Utilization
  • Get Involved
    • Donate
    • Be a Volunteer
    • Be a Member
    • CCDHS
    • Vacancy
    • Procurement
  • Media Hub
    • News
    • Publication
    • Feature Stories
    • Events
    • Gallery
      • Photos
      • Videos
  • Get help
    • Restoring Family Links
    • Ambulance Services
    • E-Learning
    • Mobile App
  • Contact

ማኅበሩ የዓለም የአእምሮ ጤና ቀንን አከበረ

ማኅበሩ የዓለም የአእምሮ ጤና ቀንን አከበረ
October 11, 2025NewsNews

አቶ ሳሙኤል አበበ የሰው ሃብት፣ ንብረት አስ/ጠ/አ/መምሪያ ኅላፊ ተወካይ

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር  በየዓመቱ በመላው ዓለም መስከረም 30 ቀን የሚከበረውን የዓለም የአእምሮ ጤናቀን የማኅበሩ አመራር አካላት፣ ሠራተኞች፣ በጎ ፈቃደኞች፣ የእህት ብሔራዊ ማኅበራት እንዲሁም የዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ እና የአለም አቀፉ ቀይ መስቀልና ቀይ ጨረቃ ማኅበራት ፌዴሬሽን ተወካዮች  በተገኙበት ‘‘የአገልግሎት ተደራሽነት ፡የአእምሮ ጤና በአደጋዎችና በድንገተኛ ሁኔታዎች’’ በሚል መሪ ቃል ተከብሯል፡፡ዕለቱ ማኅበሩ የአዕምሮ ጤናን የአደጋ ዝግጁነትና መልሶ ማቋቋም ተልዕኮዎቹ ዋና አካል አድርጎ እንዴት ቅድሚያ ሰጥቶ መስራት እንደሚገባው ለመወያየት ወሳኝ አጋጣሚ እንደሆነ ነው የተገለጸው፡፡

የማኅበሩ የሰው ሃብት፣ ንብረት አስተዳደርና ጠቅላላ አገልግሎት መምሪያ ኅላፊ ተወካይ የሆኑት አቶ ሳሙኤል አበበ በመክፈቻ ንግግራቸው እንዳሉት፣ ማኅበሩ ከ2010 ዓ.ም ጀምሮ በተወሰኑ ክልሎች የአእምሮ ጤና ተግባራትን ሲያደርሰ መቆየቱን አስታውሰው፣ የእእምሮና የስነልቦና ጤና ድጋፉን ቀሰ በቀስ ስርዓታዊ በሆነ መንገድ ወደ ብሔራዊ መስሪያ ቤትና ወደ ከልል ቅርንጫፎቻችን  በማዋሃድ ተደራሽነትን እያሰፋ ነው ብለዋል፡፡

አቶ ሳሙኤል አክለውም፣ ማኅበሩ በአሁኑ ወቅት በአብዛኛው በአደጋ ምላሽና ፍልሰት ፕሮግራሞቹ ውስጥ ማኅበረሰብ ተኮር የአእምሮ ጤናና ስነልቦናዊ ድጋፍ ለተጋላጭ የህብረተሰብ ክፍሎች እየሰጠ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

የዘንድሮው መሪ ቃል የአዕምሮ ጤና ችግሮች በብዛት ሊከሰቱባቸው የሚችሉባቸውን አካባቢዎች ለማጉላት፤ ከእነዚህ ተጎጂዎች መካከል ብዙዎቹ ሙያዊ የአእምሮ ጤና ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸውና አስፈላጊው ድጋፍ ወደ እነርሱ መድረስ እንዳለበት ለማሳየት ይረዳልም ብለዋል፡፡

አቶ አዲሱ አለባቸው የአእምሮ ጤናና የስነ ልቦና ድጋፍ ፕሮጀክት አስተባባሪ

የአእምሮ ጤና ድጋፍ በዓለም አቀፍ ደረጃ የገንዘብ ድጋፍ ዕጥረት ቀውስ እንደገጠመው ያነሱት በማኅበሩ የአእምሮ ጤናና የስነ ልቦና ድጋፍ ፕሮጀክት አስተባባሪ የሆኑት አቶ አዲሱ አለባቸው፣ በዓለም ላይ ካለው አጠቃላይ የጤና በጀት ውስጥ 2 በመቶው ብቻ ለአእምሮ ጤና እንደሚመደብ አስታውሰው በዚህ ምክንያትም ከግማሽ ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ዜጎች ሲያገኙ የነበረው አገልግሎት አደጋ ላይ ወድቋል ብለዋል፡፡

የአእምሮ ጤናና ስነ ልቦናዊና ማህበራዊ ድጋፍ  (MHSSS)ምርጫ ሳይሆን ህይወት አድን ተግባር ነው ያሉት አቶ አዲሱ ትኩረታችን በማህበረሰብ ደረጃ ላይ የተመሰረተ የአእምሮ ጤናና ስነ ልቦናዊና ማህበራዊ ድጋፍ መስጠትና ይህ ወሳኝ ድጋፍ ለሁሉንም ተደራሽ መሆኑን ማረጋገጥ ብለዋል፡፡

ዕለቱ በተለያዩ ትምህርታዊና አዝናኝ መርሃ መርሃ ግብሮች ተከብሯል፡፡

Calendar

October 2025
M T W T F S S
 12345
6789101112
13141516171819
20212223242526
2728293031  
« Sep    

Categories

  • News
  • News

Tag Cloud

Front Page

Contact Us

Ethiopian Red Cross Society Headquarter

+251-115-18-01-83/ +251-115-18-01-83

ercsinfo@redcrosseth.org

P.O.Box: 195

Ras Desta Dametew Avenue, Addis Ababa, Ethiopia

Quick Links

  • Donate
  • Be a Volunteer
  • Be a Member
  • Vacancy
  • Procurement
  • Partners link
  • FAQ

FOLLOW US

  • Facebook
  • YouTube
  • X
  • Telegram
  • Flickr
  • TikTok
Copyright ©2025 | All Rights Reserved
Designed and Developed By Rackmint System
X