የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር የ2017 ዓ.ም የዕቅድ አፈጻጸሙን የብሔራዊ ማኅበሩና የክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት እየገመገመ ነው፡፡ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በፕሮጀክቶች አፈጻጸም በኩል ከዕቅድ በላይ ውጤት እንደተመዘገበ የተገለፀ ሲሆን አባላትን ከማበራከትና ገቢ ከማሰባሰብ አኳያ ውስንነቶች መኖራቸው ተጠቁሟል፡፡ መድረኩን በንግግር የከፈቱት የማኅበሩ ዋና ጸሐፊ አቶ አበራ ሉሌሳ በማኅበሩ ብሄራዊና የክልል ቅርንጫፍ ፅ/ቤቶች የዕቅድና የሪፖርት አሰራር […]