የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ከእንግሊዝ ዓለም አቀፍ ተራድኦ የጋራ ብልፅግና አገራት ድርጅትጋር በመተባበር በደቡብ ወሎ ዞን ለሚገኙ የጤና ተቋማት ከ76 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸውን አምቡላንሶችና የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል። የተደረገውንም ድጋፍ በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር የደቡብ ወሎ ዞን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ለደቡብ ወሎ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አሊ መኮንን እና ድጋፍ ለተደረገላቸው ወረዳዎች የሥራ ኃላፊዎች […]

