በትግራይ ክልልተግባራዊ የተደረገው የመቋቋም አቅምን የማጎልበት ፕሮጀክት የማኅበረሰቡን ሕይወት እየለወጠ ነው

ወ/ሮ አሚና መሐመድ በትግራይ ክልል ደቡብ ምስራቅ ዞን፣ እንደርታ ወረዳ ደርጋአጀን ጣቢያ አራጉራ ቀበሌ ነዋሪ ሲሆኑ ከዛሬ አስር ዓመታት በፊት በደርጋጀን ጣቢያ በከፍተኛ ድህነት ውስጥ ከሚኖሩ እማወራዎች አንዷ ነበሩ።

የኢትዮጵያቀይ መስቀል ማኅበር ከዓለም አቀፉ የቀይ መስቀልና ቀይ ጨረቃ ማኅበራት ፌዴሬሽን (IFRC) እና ከሌሎች የቀይ መስቀል እህት ብሄራዊ ማኅበራት ጋር በመተባበር ለወ/ሮ አሚና በ2001ዓ.ም የወደ 25 ሺህ ብር የሚጠጋ የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል፡፡ ይህም በከብት ማድለብ ስራ እንዲሰማሩ አስችሏቸዋል። ዛሬ ላይ የአንድ ሱቅ እና የሁለት በሬዎች ባለቤት የሆኑት ወይዘሮ አሚና በዓመት ከ80,000 ብር በላይ ገቢ በማግኘት ቤተሰባቸውን ይመግባሉ፤ ያስተዳድራሉ።

“ወደ ከብት ማደለብ ስራ ከመግባቴ በፊት በጣም እንቸገር ነበር፡፡ ልጆቼ የሚመገቡት አጥተው ትምህርት አቋርጠው ነበር፡፡ ስራውን ከጀመርኩ በኃላ ግን መክሰስን ጨምሮ በቀን 3 ጊዜ እንመገባለን፡፡ ፡፡ የመጀመሪያው ልጄ ዩኒቨርስቲ ገብቶ ተመርቆ ወጥቷል፡፡” ሲሉ ወ/ሮ አሚና ማኅበሩን ያመሰግናሉ፡፡
በትግራይ ክልል ደቡብ ምስራቅ ዞን እንደርታ ወረዳ 2,259 የሚገኙ ለችግር ተጋላጭ የሆኑ አባወራዎችና እማወራዎች በተቀናጀ የምግብ ዋስትና ልማት (Integrated Food Security Development or Resilience Building) ፕሮጀክት በዘላቂነት ኑሯቸውን ማሻሻል ችለዋል።
ሌላኛዋ የፕሮጅክቱ ተጠቃሚ ወ/ሮ ዘነቡ ወከሌ የተባሉ የሰባት ልጆች እናት ናቸው፡፡ እርሳቸውም እንደ ወይዘሮ አሚና የአራጉራ ቀበሌ ነዋሪና ከአስር ዓመት በፊት በደርጋአጀን ጣቢያ በከፋ ድህነት ውስጥ ከሚኖሩ ሴቶች መካከል አንዷ ነበሩ፡፡ ያኔ ወ/ሮ ዘነቡ ከማኅበሩ ባገኙት የ12,500ብር የገንዘብ ድጋፍ የወተት ላም መግዛት የቻሉ ሲሆን አሁን ላይ ቤተሰባቸውን በአግባቡ እየመገቡ ይገኛሉ፡፡

ማኅበሩ አጋሮቹን፣ የመንግስት አካላትንና የግሉ ክፍለ ኢኮኖሚ መሪዎችን ህብረተሰቡ ከምግብ ተረጂነት በማውጣት እራሱን በራሱ መመገብ የሚያስችሉ ዘላቂ ፕሮጀክቶችን እንዲደግፉ ጥሪውን ያቀርባል።
ERCS’s Resilience Building Project Changes Communities’ Lives in Tigray Region
Mrs. Amina Mohammed, a mother of two sons and three daughters, lives in Araguara kebele, Dergajen tabia, Enderta woreda, in the South Eastern Zone of Tigray region. A decade ago, she was one of the poorest women in Deragen Tabia.

With support from ERCS, together with IFRC and other sister national societies, Mrs. Amina received financial support of 140 Euros in 2009, which enabled her to engage in cattle fattening business. She now has a shop and two oxen, earning over ETB 80,000 annually, which enables her to feed her family properly.
“Before starting cattle fattening work, our lives were challenging. I couldn’t feed my children, and they were forced to drop out of school. After starting the cattle fattening work, we have been able to feed ourselves four times a day, including snacks—in the morning, at noon, in the afternoon, and at night. Now, my eldest son has graduated from the university,” Mrs. Amina said, extending her gratitude to ERCS.

Under an Integrated Food Security Development (Resilience Building) project, the livelihoods of 2,259 vulnerable households in Enderta woreda, South Eastern Zone of Tigray region, have
sustainably improved through targeted interventions and support.

Mrs. Zenebu Wekele, a mother of seven children, resides in the same area of theTigray region. A decade ago, she was among the poorest women in Deragen Tabia. ERCS provided her with ETB 12,500 in financial support, enabling her to buy a milk cow. She now properly feeds her family.
ERCS calls on partners, government, and private sector leaders to commit funding to sustainable, community-led projects and to act to help communities transition from dependence on food aid to resilience and self-sufficiency.
————————————-