President Taye Atske Silassie paid a courtesy visit to ERCS


The President of the Federal Democratic Republic of Ethiopia, H.E. Ambassador Taye Atske Selassie, on Monday paid a courtesy visit to the Ethiopian Red Cross Society’s headquarters to observe its structure and operations.

President Taye Atske Selassie, as the patron of the ERCS, met with members of the governing board, ERCS’s high management, staff, and delegates from partner organisations.

President Taye toured the society’s management office, the newly-built studio, the Emergency Operation Centre (EOC), and the ERCS-CBE joint Filwuha Building Project where he was briefed about the emergency operation system, disaster risk reduction, and the society’s project implementation capacity.

During the briefing, Abera Tola, president of ERCS, and Abera Lulessa, SG of the Society, informed President Taye about ERCS’s domestic resource mobilisation works, explaining that the efforts aim for self-reliance, as directed by the patron.

ፕሬዝዳንት አምባሳደር ታዬ አጽቀ ሥላሴ በማኅበሩ ጉብኝት አደረጉ
የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ክቡር አምባሳደር ታዬ አጽቀ ሥላሴ የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ዋና መሥሪያ ቤትን አወቃቀር እና አሠራር ለመመልከት ጉብኝት አደረጉ።

የማኅበሩ የበላይ ጠባቂ የሆኑት አምባሳደር ፕሬዝደንት ታዬ አፅቀ ሥላሴ ከማኅበሩ የአስተዳደር ቦርድ አባላት፣ ከፍተኛ አመራሮች፣ ሰራተኞች እና ከአጋር ድርጅቶች ተወካዮች ጋር ተገናኝተዋል።

ፕሬዝዳንት ታዬ የማኅበሩን የማኔጅመንት ፅ/ቤት፣ አዲስ የተገነባውን ስቱዲዮ፣ የድንገተኛ አደጋ ኦፕሬሽን ማዕከል (EOC) እና የማኅበሩ-ንግድ ባንክ ጥምር የፍልውሃ ህንፃ ፕሮጀክትን ተዘዋውረው በመጎብኘት ስለ ድንገተኛ አደጋ የአሰራር ስርዓት፣ የአደጋ ስጋት ቅነሳ እና ማኅበሩ ስለደረሰበት ፕሮጀክት የማስፈጸም አቅም ገለጻ ተደጎላቸዋል።

በገለፃው ወቅት የማኅበሩ ፕሬዝዳንት አቶ አበራ ቶላ ከማህበሩ ዋና ጸሐፊ አቶ አበራ ሉሌሳ ጋር በጋራ በመሆን ማኅበሩ በሀገር ውስጥ ሃብት የማሰባሰብ ስራን ከበላይ ጠባቂው በተሰጠው አቅጣጫ መሰረት በትኩረት በመስራት እራስን ለመቻል ጥረቶች እየተደረጉ መሆንኑ ለፕሬዝዳንት ታዬ ገልጻ አድርገዋል፡፡

