TOLL FREE NUMBER: 907

  • Donate
HealthFlex
×
  • Home
  • Who We Are
    • About us
    • Patron
    • Governance
    • Where We Work
  • What We Do
    • Disaster Risk Management
    • Peace Building
    • Volunteers & Membership
    • Image Building
    • Capacity Building
    • Resource Mobilization
  • Get Involved
    • Donate
    • Be a Volunteer
    • Be a Member
    • CCDHS
    • Vacancy
    • Procurement
  • Media Hub
    • News
    • Publication
    • Events
    • Gallery
      • Photos
      • Videos
  • Get help
    • Restoring Family Links
    • Ambulance Services
    • E-Learning
    • Mobile App
  • Contact

ማህበሩ ከኢትዮ ቴሌኮም የተደረገለትን የአምቡላንስ ድጋፍ ተረከበ

February 12, 2019
ኢትዮ ቴሌኮም 980 ሺህ ብር የሚያወጣ የአምቡላንስ ድጋፍ ለኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር አበረከተ፡፡ ድርጅቱ ሠራተኞቹን በማስተባበር አሁን ያበረከተውን አምቡላንስ ጨምሮ በተለያዩ ሰብዓዊ ተግባራት ድጋፍ ለመስጠት ከማህበሩ ጋር በትብብር እንደሚሰራ አስታውቋል፡፡
 
የካቲት 04 ቀን 2011 ዓ.ም በማህበሩ አዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በተካሄደው ርክክብ ስነ ስርዓት ላይ የተገኙት አዲሱ የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ዋና ፀሀፊ ዶ/ር መሸሻ ሸዋረጋ፣ ኢትዮ ቴሌኮም ላደረገው ድጋፍ ያላቸውን ምስጋና ገልፀው ሌሎች ተቋማትም ይህንን አርአያ እንዲከተሉ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡
 
በአሁኑ ወቅት በሀገራችን ከ10 ሚሊዮን በላይ ሰብዓዊ ዕርዳታ ፈላጊ ወገኖች መኖራቸውንና እነዚህን ተደራሽ ለማድረግ ለስድስት ወር ብቻ 1.5 ቢሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልግ የተናገሩት ዶ/ር መሸሻ፣ በዚህ ረገድ ያለውን ክፍተት ለመሙላት የማህበሩ የበላይ ጠባቂና የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፕሬዚዳንት አስተባባሪነት የሚመራ ኮሚቴ በማቋቋም ለሰብዓዊ እርዳታ የሚውል ገንዘብ ለማሰባሰብ በዝግጅት ላይ እንገኛለን ብለዋል፡፡
 
የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈፃሚ ወ/ት ፍሬህይወት ታምሩ በበኩላቸው፣ ሰብዓዊነት ትልቅ ተግባርና ኃላፊነት በመሆኑ የዚህ ዓላማ አጋር በመሆናችን ደስታ ይሰማናል ብለዋል፡፡ የተቋሙ ሠራተኞችም በየወሩ ከደሞዛቸው ከሚያደርጉት የአባልነት መዋጮ ባሻገር በበጎ ፈቃደኝነት በዓመት ሁለቴ የደም ልገሳ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል፡፡ በሀገራችን ያለውን የሰብዓዊ እርዳታ ፍላጎት ማቃለል የምንችለው ስንተባበር በመሆኑ ተቋማት ማህበራዊ ኃላፊነታቸውን ሊወጡ ይገባል ያሉት ወ/ት ፍሬህይወት ተቋማቸው ከማህበሩ ጋር ተባብሮ በመስራት በቀጣይም መሰል ድጋፎችን ማድረግ እንደሚቀጥል ገልፀዋል፡፡
 
የማህበሩ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ቦርድ አባልና የረጅም ዓመታት የቀይ መስቀል ቤተሰብ የሆኑት አርቲስት ፋንቱ ማንዶዬ፣ የኪነ ጥበብ ባለሞያዎች በሰብዓዊ ተግባር ላይ በመሰማራት የበኩላቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡
 
ኢትዮ ቴሌኮም ከ20 ዓመት በፊት በ1000 ብር የድርጅት አባልነት መዋጮ ጀምሮ በየዓመቱ በማሳደግ ከ2008 ዓ.ም ጀምሮ በዓመት ለማህበሩ 100 ሺ ብር ድጋፍ የሚያደርግ ሲሆን ከ15000 በላይ ሰራተኞቹ ደግሞ የቀይ መስቀል መደበኛ አባል በመሆን በወር ከ30 ሺ ብር በላይ ድጋፍ ያደርጋሉ፡፡ በተጨማሪም የተቋሙ ሠራተኞች ማህበር እንደተቋም አባል በመሆን በየዓመቱ የ50 ሺህ ብር ድጋፍ ያደርጋል፡፡
 
የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ከሚሰጣቸው ሰብዓዊ አገልግሎቶች መካከል ነፃ የ24 ሰዓት የአምቡላንስ አገልግሎት አንዱ ሲሆን በዓመት በአማካኝ በአንድ አምቡላንስ ለ3600 ሰዎች አገልግሎት ይሰጣል፡፡

Calendar

February 2019
M T W T F S S
 123
45678910
11121314151617
18192021222324
25262728  
« Jan   Mar »

Categories

  • News

Tag Cloud

Front Page

Contact Us

Ethiopian Red Cross Society Headquarter

+251-115-18-01-83

ercsinfo@redcrosseth.org

P.O.Box: 195

Ras Desta Dametew Avenue, Addis Ababa, Ethiopia

Quick Links

  • Donate
  • Be a Volunteer
  • Be a Member
  • Vacancy
  • Procurement
  • Partners link
  • FAQ

FOLLOW US

  • Facebook
  • YouTube
  • X
  • Telegram
  • Flickr
Copyright ©2025 | All Rights Reserved
Designed and Developed By Rackmint System
X