TOLL FREE NUMBER: 907

  • Donate
HealthFlex
×
  • Home
  • Who We Are
    • About us
    • Patron
    • Governance
    • Where We Work
  • What We Do
    • Disaster Risk Management
    • Peace Building
    • Volunteers & Membership
    • Image Building
    • Capacity Building
    • Resource Mobilization
  • Get Involved
    • Donate
    • Be a Volunteer
    • Be a Member
    • CCDHS
    • Vacancy
    • Procurement
  • Media Hub
    • News
    • Publication
    • Events
    • Gallery
      • Photos
      • Videos
  • Get help
    • Restoring Family Links
    • Ambulance Services
    • E-Learning
    • Mobile App
  • Contact

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ሁለተኛውን የአምቡላንስ ስምሪት ማዕከል ከፈተ

May 18, 2020

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ውስጥ ሁለተኛውን የአምቡላንስ አገልግሎት መስጫ የስምሪት ማዕከል ግንቦት 06 ቀን 2012 ዓ.ም በይፋ ጀምሯል፡፡ የአገልግሎት መስጫ የስምሪት ማዕከሉ በክፍለ ከተማው ወረዳ 09 ውስጥ የሚገኝ ነው፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ አዲስ የተጨመረው የአምቡላንስ ስምሪት ማዕከል ማኅበሩ በአዲስ አበባ ከተማ ያሉትን የስምሪት ማዕከሎች ወደ ስድስት ከፍ የሚያደርገው ሲሆን ይህም ተደራሽነቱን በማስፋት የአምቡላንስ አገልግሎት ፈላጊ ህብረተሰባችንን በቅርበት ለማገልገል ያስችላል ተብሏል፡፡

ማኅበሩ በስምሪት ማዕከሉ አገልግሎት የሚሰጠውን አምቡላንስ ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ ግዢ በመፈፀም የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ አስራት ንጉሴ በተገኙበት አስጀምሯል፡፡ የአምቡላንሱን ወጪዎች ክፍለ ከተማው የሚሸፍን ሲሆን አምቡላንሱ በማኅበሩ የሚተዳደር ይሆናል፡፡

በሥነ-ስርዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ አስራት ንጉሴ፣ ክፍለ ከተማው ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው በርካታ የህብረተሰብ ክፍሎች ያሉበት ስለሆነ የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ለዚህ የሚያግዝ የአምቡላንስ አገልግሎት ከሰላሳ ዓመት በኋላ ለሁለተኛ ጊዜ በማበርከቱ አመስግነዋል፡፡ አምቡላንሱን ለታለመለት አገልግሎት በማዋል ህብረተሰባችንን በቅንነት ማገልገል ይገባል ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር አዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አበባው በቀለ በበኩላቸው፣ ማኅበሩ በክፍለ ከተማው ያለው የአምቡላንስ አገልግሎት ፈላጊ ህብረተሰብ ቁጥር ከፍተኛ መሆኑን በመረዳት ከዚህ በፊት ከነበረው አንድ የስምሪት ማዕከል በተጨማሪ ሌላ ማዕከል ከአንድ አምቡላንስ ተሸከርካሪ ጋር በመመደብ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን በመናገር ለተግባሩ ውጤታማነት የክፍለ ከተማው አመራሮች ላደረጉት ትብብር ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡ ማኅበሩ የአምቡላንሶችን ቁጥር መጨመር ብቻ ሳይሆን አገልግሎት የሚሰጡትን ባለሙያዎችና በጎፈቃደኞች በበቂ ሁኔታ በማሰልጠን ህብረተሰባችንን በአገልግሎታችን ለማርካት ይሰራል ብለዋል፡፡

በዕለቱ የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ አስራት ንጉሴ፣ ማኅበሩ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል እያካሄደ ባለው የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሀ ግብር ላይ በመሳተፍ በክፍለ ከተማው ዋና ዋና እና ሰው በሚበዛባቸው ሥፍራዎች በመዘዋወር ህብረተሰቡ የቫይረሱን መከላከያ መንገዶች ተግባራዊ በማድረግ ራሱንና ቤተሰቡን ከዚህ አስከፊ በሽታ እንዲጠብቅ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡ በሽታውን ለመከላከልና በአሸናፊነት ለማለፍ በጋራ መቆም፣ በጋራ መስራት፣ በመተባበርና ያለንን በማካፈል ሁላችንም ርብርብ ማድረግ ያስፈልገናል ብለዋል፡፡ ከግንዛቤ ማስጨበጫው ጎን ለጎን የህብረተሰቡን እጅ በአልኮል የማስታጠብና ሳኒታይዘር ለህብረተሰቡ የማከፋፈል ሥራ አከናውነዋል፡፡

በተጨማሪም በዕለቱ ማኅበሩ በክፍለ ከተማው በተለምዶ ቃሊቲ ቶታል በሚባለው ሥፍራ ለህብረተሰባችን የታክሲ አገልግሎት በሚሰጡ ተሸከርካሪዎች ላይ የፀረ ተዋሲያን ኬሚካል ርጭት አካሂዷል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ ማኅበሩ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል እየተደረገ ያለውን ጥረት የሚያግዙ አስር ከ500-1000 ሊትር መያዝ የሚችሉ የውሃ ታንከሮች (ሮቶዎች) ከዎርልድ ፋይበር እና ዎተር ኢንጅነሪንግ ተቋም ተበርክቶለታል፡፡ ታንከሮቹን በከተማዋ የተለያዩ ቦታዎች ውሃ ሞልቶ በማስቀመጥ ለህብረተሰባችን የእጅ መታጠብ ሂደት አገልግሎት እንዲሰጡ ይደረጋል፡፡

Calendar

May 2020
M T W T F S S
 123
45678910
11121314151617
18192021222324
25262728293031
« Apr   Aug »

Categories

  • News
  • Uncategorized

Tag Cloud

Front Page

Contact Us

Ethiopian Red Cross Society Headquarter

+251-115-18-01-83

ercsinfo@redcrosseth.org

P.O.Box: 195

Ras Desta Dametew Avenue, Addis Ababa, Ethiopia

Quick Links

  • Donate
  • Be a Volunteer
  • Be a Member
  • Vacancy
  • Procurement
  • Partners link
  • FAQ

FOLLOW US

  • Facebook
  • YouTube
  • X
  • Telegram
  • Flickr
Copyright ©2025 | All Rights Reserved
Designed and Developed By Rackmint System
X