19ኛው የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ጠቅላላ ጉባዔ ተካሄደ
July 29, 2022
“ያለፉት ሦስት አመታት ሕዝባችንና አገራችን ከፍተኛ ችግር ውስጥ የነበርንበትና እና ከዚህም ውስጥ ለመውጣት በጋራ ትግል ያደረግንበት ወቅት ነው፡፡ በዚህ ጉዞ ውስጥ የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ግንባር ቀደም ሚና እየተጫወተ ይገኛል፡፡ የዜጎችን ህይወት ታድጓል፣ የተከፉትን፣ ልባቸው የተሰበረ ቤተሰቦችን አንገት ቀና ለማድረግ ችሏል፡፡” ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ፣ የማኅበሩ የበላይ ጠባቂ በጉባዔው መክፈቻ ላይ ካደረጉት ንግግር (ሐምሌ 9/2014) በጠቅላላው ጉባዔ ላይ በተደረገው የአመራር ቦርድ አባላት ምርጫ አምስት በድጋሚ፣ አራት አዲስ ተመርጠዋል፡፡ በድጋሚ የተመረጡት የማኅበሩ ፕሬዚዳንት አቶ አበራ ቶላ ቀደም ሲል ባደረጉት የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር፡- “የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ሁልጊዜ ቅድሚያ ለሰብኣዊነት የሚለውን መርህ አጥብቆ ያራምዳል፡፡ በዚህ መርህ ዙሪያ ያጠነጠነ ክንውንም ያደርጋል፡፡ ለምናደርገው መልካም ነገር፣ ለሚሰማን ፍቅርና መልካም ስሜት እንዲሁም በደስታና ፍሰሃ የሚሞላውም የኛ አእምሮና አካል ነው፡፡ ለዚህም የተሳካ ጉዞ የማህበሩ ሰራተኞች፣ በጎፈቃደኞች፣ አባላት፣ መንግስት፣አጋሮቻችን፣ የቀይ መስቀልና ቀይ ጨረቃ ንቅናቄ አካላት ዋናዎቹ የስኬታችን ባለቤቶች ናቸው፡፡ “ ብለዋል፡፡ ጠቅላላ ጉባዔው ላይ 250 ተሳታፊዎች የተገኙ ሲሆን 173 ቱ ከክልል የቀይ መስቀል ቅርንጫፎች የመጡ ናቸው፡፡ ማኅበሩን ለሚቀጥሉት አራት አመታት እንዲመሩ የተመረጡት የኢቀመማ የአመራር ቦርድ አባላት የሚከተሉት ናቸው፡
1. አቶ አበራ ቶላ፣ ፕሬዚዳንት
2. ዶ/ር ፎዚያ አሚን፣ ምክትል ፕሬዚዳንት
3. ወ/ሮ ሒክመት አብደላ፣ አቃቤ ነዋይ
4. ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ፣ አባል
5. ፕሮፌሰር አብርሃም ኃ/አምላክ፣ አባል
6. አምባሳደር ዶ/ር ቶፊቅ አብዱላሂ፣ አባል
7. ዶ/ር አዲስአለም ሙላት፣ አባል(የወጣቶች ተወካይ)
8. ኢንጂነር ጌታሁን ሁሴን፣ አባል
9. ዶ/ር ሰይፉ ጌታሁን፣ አባል




