ኢትዮጵያዊያን የህክምና ባለሙያዎች በሰሜን አሜሪካ ሰብዓዊ ዕርዳታ አደረጉ
‘’ሐኪም ወርቅነህ፣ መላኩ በያን በሰሜን አሜሪካ የሕክምና ባለሙያዎች ማzበር’’ የ10,000 (አስር ሺ የአሜሪካን ዶላር) የገንዘብ እርዳታ ለኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማzበር ሰጠ፡፡ ዶ/ር ዘርጋባቸው አስፋው የማzበሩ ኘሬዚደንት በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ብሔራዊ ጽ/ቤት ተገኝተው የገንዘቡን ደረሰኝ አስረክበዋል፡፡
አቶ ጌታቸው ታዓ፣ የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማzበር ዋና ፀሐፊ ማzበሩ በግጭት ለተጐዱ ተረጂዎቻችን ላደረጉት የገንዘብ እርዳታ አመስግነዋል፡፡
ዶ/ር ዘርጋባቸው በገቡት ቃል መሠረት፣ የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል የእድሜ ልክ አባል በመሆን በሰሜን አሜሪካ ለሰብዓዊነት በይበልጥ እንደሚሠሩ ገልጸዋል፡፡
ፋሺስት ጣሊያን ኢትዮጵያን በ1927 ዓ.ም በወረረችበት ወቅት የሐኪም ወርቅነህ ሁለት ልጆች ቢኒያምና ዮሴፍ ወርቅነህ ከእንግሊዝ አገር መጥተው፣ እንዲሁም ዶ/ር መላኩ በያን ከአሜሪካ አገር መጥተው የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማzበር በጐ ፈቃደኞች በመሆን አገልግለዋል፡፡ ሁለቱም የሐኪም ወርቅነህ ልጆች የካቲት 1929 የፋሺስት ጭፍጨፋ ሰለባ በመሆን ውድ ህይወታቸውን ለአገራቸው ሰውተዋል፡፡
መላኩ በያን ወደአሜሪካ ተመልሰው ህይወታቸው እስካለፈበት ሚያዝያ 26 ቀን 1932 ዓ.ም ድረስ ሰብዓዊ እርዳታ በማሰባሰብ ለኢትዮጵያ ይልኩ እንደነበር ከኢትዮጵያ የቀይ መስቀል ማzበር ታሪክ መጽሐፍ ለመረዳት ተችሏል፡፡